info@merkeznurah.info +2519-11-42-89-20

መዕከሉ ለአቅመ ደካሞች ያደረጋቸው ሰብኣዊ እገዛዎች

ሰብኣዊ እገዛዎች

1.በ 2011 በአካባቢው ለሚገኙ 300 አቅመ ደካሞች እና የጠቀር ቀበሌ በጎርፍ ለተጎዱ 300 ወገኖች በአጠቃላይ ለ600 ወገኖች የረመዳን ሙሉ ወር የኢፍጣር ፕሮግራም

2.በዛው አመት 2011 በዒድ አል አድሃ በዓል ለ475 ቤተሰቦች የኡዱሂያ ስጋ የማከፋፈል ስራ

  • 3. በ 2012 በዒድ አል አድሃ በዓል 47 በኤች አይ ቪ ለተጠቁ ወገኖች እንዲሁም ከወረዳዉና ከቅበት ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ 425 ቤተሰቦች በጠቅላላ ለ472 ቤተሰቦች የኡዱሂያ ስጋ የማከፋፈል ስራ
  • 4.በ2013 መርከዙ በተመሰረተበት አካባቢ ለሚገኙ ከ300 በላይ አቅመ ደካሞች በኑራህ መስጂድ እንዲሁም በቀበሌው በሚገኘው ፈትህ መስጂድ ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ከ300 በላይ አቅመ ደካሞች ሙሉ የረመዳን ወር የኢፍጣር ፕሮግራም
  • 5.በ2013 ዒድ አል አድሃ በዓል ከቅበት ከተማ አስተዳደር፤ከሰነና ገሬራ ቀበሌ እና ከዶቦ ሳቦላ ቀበሌ ለተውጣጡ ከ260 በላይ አቅመ ደካማ አባወራዎች በአጠቃላይ 700 ለሚሆኑ የቤተሰብ አባላት የኡዱሂያ ስጋ የማከፋፈል ስራ

በአላህ ፍቃድ በአጭር እና በረጅም ጊዜ የታቀዱ ስራዎች እና ፕሮጀክቶች

01

የተማሪዎች እና የኡስታዞች ማደሪያ

የተማሪዎች እና የኡስታዞች ማደሪያ ...

02

ለተለያዩ ፕሮግራሞች የሚሆን አዳራሽ

ለተለያዩ ፕሮግራሞች የሚሆን አዳራሽ ....

03

ከአፀደ ህፃናት ጀምሮ እስከ 4ኛ ክፍል መማሪያ

ከአፀደ ህፃናት ጀምሮ እስከ 4ኛ ክፍል መማሪያ ....

04

አካዳሚክ ላይብረሪ

አካዳሚክ ላይብረሪ ...

05

የወጣቶች መዝናኛ መዕከል

የወጣቶች መዝናኛ መዕከል ....

06

የመጠጥ ውሃ ቁፋሮ እና ዝርጋታ

ከሚመለከታው አካል በጋራ በመሆን የመጠጥ ውሃ ቁፋሮ እና ዝርጋታ፤የመብራት ዝርጋታ እና የተለያዩ ህብረተሰብ አቀፍ የሁኑ ልማቶች ለማልማት እቅድ ተይዟል፡፡

የተጠናቀቁ ግንባታዎች

ታላቅ የምስራች ለቁርኣን ሂፍዝ ፈላጊዎች

ኑራህ የቁርኣን እና የሀዲስ ሂፍዝ ማዕከል በቅበት ከተማ አስተዳደር በ2ኛ ዙር የሂፍዝ ፕሮግራም መደበኛ እና ተመላላሽ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ያለን ቦታ ውስን በመሆኑ ፈጥነው በመመዝገብ የእድሉ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ተጋብዘዋል፡፡

የሂፍዝ ማዕከሉ የሚሰጣቸው የትምህርት ዘርፎች

1. አዲስ የቁርኣን ሂፍዝ

2. የቁራኣን ኢጃዘህ እና ሰነድ መስጠት

3. አጫጭር የዐቂዳ ኪታቦች እና የአርበዒን ሀዲስ ሂፍዝና ትንታኔ

4. የፊቂህ ትምህርቶች እንዲሁም ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ት/ቶችን ያስተምራል፡፡

መደበኛ ተማሪዎች ማሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

1.እድሜያቸው ከ17 ዓመት በላይ የሆኑ ተማሪዎች ወላጅ፤የቀበሌ መታወቂያ እና የተዝኪያ ወረቀት ይዞ መምጣት

2.እድሜያቸው ከ17 ዓመት በታች የሆኑ ተማሪዎች ወላጅ እና የወላጅ የፍቃድ ወረቀት ይዞ መምጣት

3.የመግቢያ ፈተናውን ማለፍ የሚችል እንዲሁም አጠቃላይ የሂፍዝ ማዕከሉን ህግ እና ደንብ የሚያከብር

መዕከሉ ያከናወናቸው የህብረተሰብ ፕሮግራሞች

በ2012 የቁርኣንና የሀዲስ ሂፍዝ ፕሮግራም በቅርንጫፍ መልኩ በቅበት ከተማ አስተዳደር ግዚያዊ ቤት በመከራየት የቁርኣን ኢጃዛ ፕሮግራም፤ሀፍዘው ለረሱ የሙራጀዓ ፕሮግራም፤አዲስ የቁርኣን ሂፍዝ ፕሮግራም፤አጫጭር የዐቂዳ ኪታቦች ሂፍዝ እና ትንታኔ ፕሮግራም፤የሀዲስ እና የፊቂህ ትምህርት ሂፍዝ እና ትንታኔ ፕሮግራም፤የቱህፈቱል አጥፋል መትን ሂፍዝ ፕሮግራም 17 መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል በመጀመሪያ ዙር ሙሉ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 10 ተማሪዎች በተሰጣቸው ፕሮግራም መሰረት ሙሉ 30 ጁዝ ቁርኣን፤ሙሉ አርበዒን ሀዲስ፤ኡሱሉ ሰላሳ እና ቀዋዒዱል አርበዕ፤ኪታቡ ተውሂድ 15ኛ ምዕራፍ ድረስ እንዲሁም ቱህፈቱል አጥፋል 16ኛ ስንኝ ድረስ ሀፍዘው በመጨረስ የተዘጋጀላቸውን ሰርተፊኬት የሚያገኙ ሲሆን ቀሪዎቹ በቀጣዩ ዙር ወደ መርከዙ የሚገቡ ይሆናል፡፡

  • All
  • መስገጃ ቦታ እና ምርቃት
  • የኡዱሂያ
  • የተማሪዎች መማሪያ

መስገጃ

ተማሪዎች

Videos

Contact

የኑራህ መስጂድ እና መድረሳ መዕከል:

በስልጤ ዞን በስልጢ ወረዳ ሰነና ገሬራ ቀበሌ መንደር 4 ልዩ ስሙ ኮራሜ

Call:

+1 5589 55488 55s

Loading
Your message has been sent. Thank you!